ገብተዋል ስለተባሉት ስደተኞች እውቅና እንደሌለው የጋምቤላ ክልል አስታወቀ

Date:

በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በተባባሰው ግጭት ምክንያት ከደቡብ ሱዳን ሸሽተው በጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን ማታር ገብተዋል ስለተባሉት ስደተኞች እውቅና እንደሌለው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለአሐዱ ገልጿል፡፡

ከሰሞኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን በመንግሥት ወታደሮችና በአማፂዎች መካከል የሚደረገውን ግጭት በመሸሽ በክልሉ በመጠለላቸው ምክንያት፤ ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) በርቤይ በምትባል የድንበር ከተማ የነበረውን የሕክምና ማዕከል ወደ ጋምቤላ ክልል ማዛወሩን መግለጹ ይታወሳል።

ተፈናቃዮቹ በደቡብ ሱዳን የሕዝቦች መከላከያ ኃይሎችና በተቃዋሚ ቡድን መካከል በተፈጠረው ውጊያ ምክንያት የአየር ላይ ጥቃቶችን በመሸሽ መሰደዳቸው የተገለጸም ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ በጋምቤላ ክልል ማታር ከ35 ሺሕ እስከ 85 ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙም ተነግሯል።

ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) “የአካባቢው መሠረተ ልማቶች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እያስተናገዱ ነው” ያለ ሲሆን፤ ምርመራ ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከልም 40 በመቶዎቹ የወባ በሽታ ተጠቂ መሆናቸውን በመረጃው አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ሕጻናት መካከል ወደ 7 በመቶ የሚጠጉት ከባድ የአጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምልክቶች እንደታዩባቸዉ የገለጸው የሐኪሞች ቡድኑ፤ እርጉዝ እና የሚያጠቡ ሴቶች መካከል ደግሞ የአጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጠን ከ14 በመቶ በላይ መሆኑን አስታውቋል።

በመሆኑም ስደተኞቹ የውሃ እጥረትን ጨምሮ በርካታ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን በመግለጽ፤ ወሳኝ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶቹን በመያዝ ከበርቤይ ወደ ማታር ማዘዋወሩን አስታውቋል።

አሐዱም “ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች በክልሉ በምን አይነት መልኩ እየተገለገሉ እንደሚገኝና አጠቃላይ ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል?” ሲል ክልሉን ጠይቋል።

የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኦጁሉ ጊሎ በሰጡት ምላሽ፤ በቅርቡ ወደ ክልሉ ስለገቡት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መረጃን በተመለከተ በመንግሥት ደረጃ እውቅና እንደሌላቸው ገልጸዋል።

በመሆኑም የዚህ ጉዳይ መረጃ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) እና መሰል ተቋም እጅ ላይ ብቻ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አክለውም አጠቃላይ ምን ያክል ስደተኞች እንደገቡና የት የት ቦታ እንደተጠለሉ እንዲሁም የት መጠለል እንደሚገባቸው ጨምሮ ውሳኔ የሚያሳልፋት እነርሱ እንደሆኑ ገልጸዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...