ሊቨርፑል ጄረሚ ፍሪምፖርግን ከባየር ሊቨርኩሰን አስፈረመ

Date:

ሊቨርፑል የባየር ሊቨርኩሰኑን የቀኝ መስመር ተከላካይ ጄረሚ ፍሪምፖንግን በ30 ሚሊዮን ዮሮ የዝውውር ሂሳብ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ። 

በስምምነቱ መሠረት ፍሪምፖንግ በሊቨርፑል ቤት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።

ሊቨርፑል የአንፊልዱ ኮከብ ትሬንት አሌክሳንደር ወደ ማድሪድ መቀላቀሉን ይፋ ካደረገ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ኔዘርላንዳዊውን ኢንተርናሽናል ተጫዋች ማስፈረሙን  አረጋግጧል።

ሁለገቡ የቀኝ እግር ተጫዋች ፍሪምፖንግ በአርኔ ስሎት ቡድን ውስጥ የአሌክሳንደር አርኖልድ ምትክ ሆነው ይጫወታሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሆኗል።

በልጅነቱ በማንቸስተር ሲቲ ቤት ሰልጥኖ ያደገው ሆላንዳዊው በ2021 ወደ ሊቨርኩሰን ከመዛወሩ በፊት በ2019 ለሴልቲክ ተጫውቷል።

ፍሪምፖንግ በሊቨርፑል ቤት የሀገሩ ኮከቦች ከሆኑት ቨርጂል ቫን ዲጅክ፣ ኮዲ ጋክፖ እና ራያን ግራቨንበርች ጋር ተቀላቅሏል።

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...