አሐዱ ባንክ ከኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓል ንዋዮች ገበያ ባለሥልጣን ጋር ውጤታማ ውይይት አደረገ

Date:

ባንክ የቦርድ ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ሰብስቤ፣ የቦርድ አመራሮችን እና የማኔጅንት አባላት በተገኙበት ከኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓል ንዋዮች ገበያ ባለሥልጣን መ/ቤት (Ethiopian securities Exchange) ከመጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት ሐመር አዳራሽ ግንቦት 22/2017 ዓ.ም ውጤታማ ውይይት አደረጉ::

ከኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓል ንዋዮች ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ጥላሁን እስማኤልን ጨምሮ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች የሰነድ ሙዓል ንዋዮች ገበያ ምንነት፣ እንዴት እንደሚሰራና ባንኮች ከዚህ ተቋም ጋር ቢሰሩ በምን ዓይነት መልኩ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ሰፊ ማብራሪያዎች በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎች አማካይነት ተሰጥቷል፡፡ ውይይቱን ተከትሎ በባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ቀርበው የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የአሐዱ ባንክ የቦርድ ዳሬክተር አቶ አንተነህ ሰብስቤ እንደገለጹት የሰነድ ሙዓል ንዋዮች ገበያ (Securities Exchange) የፋይናንስ ተቋማትን የማሳደግ አቅም ያለው እንደሆነና ፤ አሐዱ፡ባንክም ተተኳሪ ቡድን ተቋቁሞ በቦርድ ደረጃ የቅድመ-ዝግጅትና የጥናት ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል::

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...