7ኛው ዓለም አቀፍየአግሮ ፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

Date:

የምግብና መጠጥ ግብዓቶች ቴክኖሎጂና የፕላስቲክ ውጤቶች ለዕይታ የሚቀርቡበት 7ኛውዓለም አቀፍ የአግሮ ፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

‌‎ፕራና ኢቨንትስ ከጀርመን አጋሩ ፌርትሬድ ጋር በመተባበር 7ኛውን “አግሮ ፉድ እና ፕላስት
ፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ” ዓመታዊ የንግድ ትርዒት ያዘጋጁት ሲሆን፥ ከመጪው ሰኔ 12 እስከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ታውቋል።

‌‎የንግድ ትርዒቱ ዓለም ዓቀፍ የግብርና፣ የምግብና መጠጥ ግብዓቶች እና ቴክኖሎጂ፥ እንዲሁም የፕላስቲክ፣
የህትመትና የማሸጊያ ቴክኖሎጂና ምርቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።

‌‎ለሦስት ቀናት በሚቆየው የንግድ ትርዒት ላይ ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ140 በላይ አውደ ርዕይ አቅራቢዎች ለኢትዮጵያ ገበያ የሚስማሙ ምርቶችንና መፍትሄዎችን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

‌‎ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከኦስትሪያ፣ ቻይና፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ዮርዳኖስ፣ኬንያ፣ ፖላንድ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ታይዋን፣ ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የተውጣጡ ከ130
በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።
‌‎
እነዚህ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ገበያ ተብለው የተዘጋጁ ምርቶችን እና አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ መጠጥ አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር የሚዘጋጁ
የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱም ተመላክቷል።

@Arada_Fm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...