ኦነግ እና ኦፌኮ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችል አቋም ላይ እንዳልኾኑ መናገራቸውን ቢቢሲ ኦሮሚኛ ዘግቧል። ፓርቲዎቹ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱት ግጭቶች ብቻ ምርጫውን ላለማድረግ በምክንያትነት ሊጠቀሱ እንደሚችሉ መጥቀሳቸውን ዘገባው አመልክቷል።
ፓርቲዎቹ፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሕዝባዊ ውይይቶችንና የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይችሉና መንግሥት ከፍተኛ ጫና እንደሚያደርስባቸው ገልጸዋል ተብሏል።
የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ነባር ችግሮች ሳይፈቱ ምርጫ ከተሄደ አገሪቱን ወደባሰ ትርምስ ይከታታል በማለት ማስጠንቀቃቸም በዘገባው ተጠቅሷል። ቦርዱ ለምርጫው ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መኾኑንና ምርጫውም በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ እንደሚያከናውን ሰሞኑን አስታውቆ ነበር።
