የ3ኛው ፓትርያርክ የዕረፍት መታሰቢያ

Date:

የዛሬ 37 ዓመት

ግንቦት 28/ 1980 ዓ/ም  የ3ኛው ፓትርያርክ  የዕረፍት መታሰቢያ

ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ተ/ሃይማኖት ፓትርያርክ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ዘኢትዮጵያ፡፡

ሢመት ፡ ሰኔ  30 : 1968: ጵጵስና  ነሐሴ 23 /1968 ፕትርክና ተሹመዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ከሾሟቸው አባቶች መካከል   ሁለቱ ፓትርያርኮች  ሆነዋል።

+ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ
+ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በብዙ ጾምና ጸሎት  አብዝተው መንበሩን አክብረው ይኖሩ ነበር፡፡

ቤተ ክርስቲያን  ከጠላት መንጋጋ  ለይተው ጠብቀዋል፡፡

የተሻሉ አሠራሮች  ቤተ ክርስቲያን እንዲቀጥሉ (ሰበካ ጉባኤ ተግባር ላይ እንዲወርድ) ፡ 36 ሕጻናት ማሳደጊያ  ጣቢያዎች   ተክለዋል ፡፡

ለቤተ ክርስቲያን መሾም ማለት ሥልጣን ሳይሆን ኃላፊነት፡ ዕዳ  መሆኑን  በሚነበብ ሕይወታቸው  ዘግበዋል፡፡

በ12 ጊዜ  ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት  28 አባቶችን ሾመዋል፡፡

ዛሬ ላይ በሕይወተ ሥጋ ያሉ የመንጋው ባላደራዎች 6 ናቸው፡፡

1.ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ =1971 ዓ/ም
2.ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ =1971 ዓ/ም
3.ብፁዕ አቡነ ኤልያስ = 1973 ዓ/ም
4.ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ   =1977 ዓ/ም
5.ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ =1979 ዓ/ም

  1. ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ =1979 ዓ/ም

ቅዱስነታቸው ግንቦት 28 ቀን  በአካለ ሥጋ ተለይተው ግንቦት 30/1980 ዓ/ም  ሥርዓተ ቀብራቸው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

             በረከታቸው ይደርብን

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
  ሐዋርያት ፳፥፳፰

©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...