የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት

Date:

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በ”ኬኛ ቤቭሬጅስ” ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሶስት ነገሮች ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም አንደኛው የመጣውን ድል መጠበቅ፣ ማቆየት እና ማሻገር  ነው ብለዋል።

ሁለተኛ ልማት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

”ልማት ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምንም ሳያጓድል ለህዝቡ የገባውን ቃል እየተወጣ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሶስተኛውን ግን አልተናገሩትም፡፡

”የእምቢተኝነቱ የመጨረሻው ትግል በሚካሄድበት ወቅት የክልሉ መንግስት ከያዛቸው ትልልቅ ውጥኖች ውስጥ እንዱ የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት ነው” ሲሉም አቶ አወሉ ተናግረዋል፡፡

”የኦሮሞ ኢኮኖሚ አብዮት 5 ትልልቅ ነገሮችን በውስጡ እንደያዘ የጠቆሙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አንዱ ኬኛ ቤሄቭረጅስ ነው፤ ሁለተኛው ኬኛ የግብርና ማሽነሪዎች አቅራቢ የሆነው በሻሸመኔ ተቋቁሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ትራክተሮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሮች እያቀረበ ያለው ነው፤ ሶስተኛው የግንባታ መዘግየትን ችግር ለመፍታት የተቋቋመው ወላቡ ኮንስትራክሽን ነው” ብለዋል።

አራተኛው ኦዳ ትራንስፖርት፣ አምስተኛው ደግሞ የአምቦ ውሃ ምርት ነው እሱንም እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡

”ኬኛ የኦሮሞ የትግል መሳርያ ብቻ ሳይሆን የትግሉ ሞተርም ነበር ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ያ የትግሉ መሳርያ የነበረው ዛሬ የትግሉ ውጤት ሆኖ እያጣጣምነው ነው” ብለዋል፡፡

”ኬኛ ቤቬሬጅስ እዚህ እንዲደርስ ብዙ ዋጋ ተክፍሏል” ያሉት አቶ አወሉ አብዲ ”በወቅቱ ንግዱ ታውኮ ነበር፤ ብድር ማግኘትም አንችልም ነበር ሲሉ አስረድተዋል፡፡

“ብዙ ባንኮች ጋር ሄደን ነበር፤ የተወሰነው ለእኛ ለማበደር ፍላጎት የለውም፤ ሌላው ደግሞ ባህሪ የለውም ፤ ቀሪው ደግሞ አቅም የለውም ነገር ግን ትልቁ ቁጠባ የተሚሰበሰበው ከእኛ ነው” ሲሉ የተናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከዚያ ተነስተን ባንክ እንደሚስፈልገን ተረዳን ከዚያም ስንቄ ባንክን አቋቋምን ብለዋል፡፡

አሁን ህዝብን እና ሀገርን ሊያገለግል የሚችል ትልቅ የሆነውን ስንቄ ባንክን አቋቁመናል ያሉት አቶ አወሉ አብዲ ይህም ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን የኦሮሞ ኢኮኖሚ አብዮት ውጤት ነው ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ኢኮኖሚ አብዮት እንዳይሳካ ብዙ ሃይሎች ሲሰሩ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም ሲያሉት  ምክትል ፕሬዝዳንቱ እነማን እንደሆኑ ግን በስም አልጠቀሱም፡፡

የኬኛ ቤቬሬጅስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ነዋይ መገርሳ በበኩላቸው ባደረጉት ንግገር ‹‹ኬኛ ልክ የዛሬ 8 ዓመታት አካባቢ የኦሮሞ የኮኖሚክ ሪቮሉሽን ብለን ጀመርን ካሳካናቸው 5 ትልልቅ ከኩባንያዎች ውስጥ ዘመናዊ  እና ወደ 250 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው›› ሲሉ  ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው አሁን ላይ ለ250 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል የተባለ ሲሆን በቀጣይ የሠራተኛውን ቁጥር ወደ 1,000 ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...