ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከአውሮፕላን አደጋ የተረፈውን ብቸኛ ተሳፋሪ ጎበኙ

Date:

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከትናንትናው የአውሮፕላን አደጋ በተዓምር የተረፈውን ብቸኛ ተሳፋሪ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

ከአደጋው የተረፈው የ40 ዓመቱ እንግሊዛዊ ቪሽዋሽ ኩመር ራምሽ በአህመዳባድ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ነው።

ቪሽዋሽ ኩመር ራምሽ ከአደጋው እንዴት እንደተረፈ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ መግለጹን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ በተፈጠረው አደጋ በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸው፤ በአደጋው ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦች መፅፅናናትን ተመኝተዋል።

ከሕንድ አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ 242 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ጉዞ ለማድረግ ከተነሳ በኋላ በሰከንዶች ውስጥ በተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ ምክንያት እስካሁን ባለው መረጃ 242 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

የህንድ የአቪዬሽን ባለስልጣን በበኩሉ ሁሉንም የቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ላይ የበረራ እገዳ ለመጣል ማቀዱ ታውቋል።

የህንድ አየር መንገድ ወደ ሰሜን አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ለሚደረጉ ረጃጅም በረራዎች እነዚህን አውሮፕላኖች የሚጠቀም ሲሆን፤ የሀገሪቱ የአቪዬሽን ባለስልጣን  ምርመራ ለማደረግ ሲባል አውሮፕላኖቹ በጊዜያዊነት ለማገድ መወሰኑን የቴሌግራፍ ዘገባ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...