የካህናትና ምእመናን ሥልጠና በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየተሰጠ ይገኛል

Date:

ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማእከል የሚገኘው በኤስድሮስ ሴሚናሪየም አዘጋጅነት በደቡባዊው አፍሪካ  የካህናትና የምእመናን ሥልጠና በእንግሊዘኛ ቋንቋ  እየተሰጠ እንደሚገኝ ማኅበረ ቅዱሳን ደቡብ አፍሪካ ማእከል ገልጿል።

ዶ/ር ሰለሞን ድሪብሳ የደቡባዊ አፍሪካ ማእከል የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ እንደገለጹት ሥልጠናው  ሁለት ዓላማዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ቦትስዋና፣ ናምቢያ፣ ሌሴቶና በሌሎችም ደቡባዊ አፍሪካ ባሉ አገራት  ሐዋርያዊ ተልእኮን ማስፈጸም እንዲቻል  በእግሊዘኛ ቋንቋ  ማስተማር የሚችሉና አዳዲስ አማንያንን አስተምሮ ማስጠመቅ እና ማጽናት የሚችሉ መምህራንን ለማፍራት ሥልጠናው እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም በማእከሉ ስር በሚገኙ አገራት ተወልደው ለሚያድጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ለደቡባዊ አፍሪካዊ ሕጻናት ልጆች እንዲሁም ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርቱን ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በሥልጠናው የመጀመሪው ዙር በ2016 ዓ.ም ሁለት ደቡባዊ አፍሪካ ካህናት በዲፕሎማ መርሐ ግብር የተመረቁ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ አራት ሠልጣኞች ማለትም አንድ በደቡባዊ ካህንና ሦስት ምእመናን እየሠለጠኑ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

በዚህም ሥልጠናው ሁለት ዓመት ተኩል የሚፈጅ የዲፕሎማ መርሐ ግብር ሲሆን በተለያየ መንገድ ማለትም በኦላይን በሳምንት ሁለት ቀን ለሁለት ሰዓትና ለተማሪዎች በተዘጋጀ Student Learning Managnment platform አማካኝነት እየተሰጠ እንደሚገኝ ዶ/ር ሰሎሞን ገልጸዋል።

የማእከሉ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊው እንዳሉት ሠልጣኞች ከሥልጠናው ባገኙት መንፈሳዊ ዕውቀት፣ ክህሎትና ጥበብ በመጠቀም አዳዲስ ምእመናን አስተምሮ ማስጠመቅና በሃይማኖት እንዲጸኑ ለማድረግ ማስተማር፣ ለአገልግሎት መሰማራት፣ ልጆችን፣ ወጣቶችን እንዲሁም ግቢ ጉባኤ ትምህርት ላይ የሚገኙትንም መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያስተምሩ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመጨረሻም ኃላፊው ሙሉ የትምህርት ወጪን በመሸፈንና ስኮላርሺፕ በመስጠት በማእከላቱ ለሚገኙ ካህናትና ምእመናን ሥልጠናው እንዲሰጥ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ለማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን አሜሪካን ማእከል እና ኤስድሮስ ሴሚናሪየምን አመስግነዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...