በመዲናዋ 44 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተከናወነ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የወንዝነት ባህሪያቸውን ለቀው የነበሩትን የመዲናዋ ወንዞች ከብክለት ለመከላከል 44 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተከናወነ ነው አለ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በባለስልጣኑ በተደረጉ ጥናቶች ወንዞቹ የተፈጥሮ መልካቸውን ለቀው ለከፍተኛ ብክለት ተጋልጠዋል፡፡

በዚህም ወንዞችን ከብክለት ለመከላከል 44 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል።

የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የህዝብ መዝናኛዎች፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ የልጆች መጫወቻዎች፣ የአትሌቶች መለማመጃዎችን እና ፓርኮችን አካቶ እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው÷ ወንዞችን ከብክለት ለመጠበቅ የወንዞች ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡

ደንቡ ወደ ወንዝ ዳርቻ ልማቱ በካይ ነገሮችን የለቀቁ ግለሰቦች እና ተቋማት ከ2 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ እንደሚቀጡ ተደንግጓልም ነው ያሉት።

(ኤፍ ኤም ሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...