እስራኤል ኢራንን በኒውክለር የምታጠቃ ከሆነ ፓኪስታን በተመሳሳይ በኒውክለር መሳሪያ በእስራኤል ላይ ጥቃት እንደምታደረስ የኢስላሚክ አብዮታዊ ዘብ ጄኔራልና የኢራን ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል ተናገሩ፡፡
ከፍተኛ የእስላሚክ አብዮታዊ ዘብ ጄኔራል እና የኢራን ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል ሞህሰን ረዛኢ ከኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸዉ ቃለመጠይቅ፤ ‹እስራኤል እኛን በኒውክለር መሳሪያ የምታጠቃ ከሆነ ፓኪስታን የአጸፋ እርምጃ በኒውክለር መሳሪያ እንደምትወስድ ቃል ገብታልናለች› ብለዋል፡፡
የፓኪስታን ሻህን -3 የተሰኘዉ ሚሳኤል 2 ሺህ 7 መቶ ኪሎሜትር ተጉዞ በእስራኤል የትኛዉም ክፍል ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም አለዉ ተብሏል፡፡
ጀነራሉ ይህን ቢሉም እስካሁን ግን በፓኪስታን ባለስልጣናት በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡
ይሁን እና ፓኪስታን የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ከኢራን ጎን መሰለፏን እየገለጸች ትገኛለች፡፡
የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ ሰኔ 14 ቀን በብሔራዊ ምክር ቤት ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሙስሊም ሀገራት በእስራኤል ላይ አንድ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
የእስራኤል ጥቃት ኢራንን ብቻ ሳይሆን የመንን እና ፍልስጤምን ጭምር ያነጣጠረ መሆኑንና አንድ አለመሆን ሁሉንም የሙስሊም ሀገራት ለተመሳሳይ ጥቃቶች ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው አስጠንቅቀዋል ታይምስ ኦፍ ኢዲያን እንደዘገባው ።
