ሁለት የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ንግግር ላይ ናቸው

Date:

ኡልያኖቭስክ እና አውቶቫዝ የአውቶሞቢል ፋብሪካዎች የሀገሪቱን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምህዳር እያጠኑ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ኢቭጌኒ ተርኪን ለሩሲያ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡

“ይህ ሂደት የፕሮጀክቶቹን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ለማረጋገጥ ጥልቅ የገበያ እና የቴክኒክ ምርምር ማድረግን ያካትታል። ድርድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ ውጤቱ የሩሲያ መኪኖች በኢትዮጵያ መንገዶች የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ ወደሚያስችሉ ውሳኔዎች እንደሚመራ እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡

🤝 በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ካሉት እጅግ ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፎች ውስጥ አንዱ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ እንደሆነ አምባሳደሩ አክለዋል።

“ወደ 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የሚይዘው ሰፊው የኢትዮጵያ ገበያ የሩሲያ አምራቾች ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ነው።”

ከሴንት ፒተርስበርግ ትራክተር ፋብሪካ የሙከራ ትራክተሮች እንደተላኩ እና “ላዳ ኤክስፖርት” የተባለው ኩባንያ ከ “ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ” ጋር የአጋርነት ግንኙነት መመስረቱም ነው የተመላከተው፡፡

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር …

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7...

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...