።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በክሪፕቶ ማይኒንግ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች በፈረንጂዎቹ DEC 1/2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን ተቋሙ ጥቅምት 17/2018 ዓም በጻፈላቸው ደብዳቤ ማሳወቁን አመልክቷል።
በደብዳቤው መሰረት የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች የታህሳስ ወር የኤሌክትሪክ ሽያጭ ሂሳብ የሚከፍሉት በተሻሻለው ታሪፍ መሰረት ይሆናል።
የተሻሻለው የታሪፍ መዋቅር የዳታ ማይኒንግ ካምፓኒዎች የኃይል ክፍያዎችን እንደ አጠቃቀም ሰአታቸው/ጊዜ(Time of use) እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን የደብዳቤውን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።
አቶ ሞገስ በሰጡን ማብራሪያ ” የታሪፍ ማሻሻያው ዝርዝር የአጠቃቀም ሰአቶች እና ታሪፍም ጭምር አለው ከእዚህ በፊት የነበረው የታሪፍ አተገባበር ፍላት ነው የአሁኑ እንደ አጠቃቀማቸው ፒክ በሆነ ሰአት እና እንደሚጠቀሙበት ሰዓት የተለያየ የክፍያ መጠን ይኖራቸዋል ” ሲሉ አስረድተዋል።
@tikvahethiopia
