የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስኬት ተሞክሮ በማካፈል “ዲጂታል ኢትዮጵያ” እውን እንዲሆን ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ።
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በንግግራቸው፤ በአሁኑ ወቅት በሕንድ እያንዳንዱ ዜጋ የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም ሙሉ በሙሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በሕንድ በዓመት ሦስት ጊዜ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የዲጂታል ፋይናንስ አጠቃቀም ድጋፍ እንደሚያገኙ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ አሠራር አገሪቱን በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ማድረጉን አመላክተዋል።
ይህንን የቴክኖሎጂ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ለማካፈል አገራቸው ዝግጁ መሆኗንም ናሬንድራ ሞዲ አረጋግጠዋል።
