ሶማሊያ እና ግብፅ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን በ ካይሮ ባካሄዱት ምክክር በድጋሜ አረጋገጡ

Date:

የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዲሰላም አሊ ከግብፅ አቻቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዴላቲ ጋር ትናንት ሐሙስ በካይሮ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ምክክር ማካሄዳቸውን የሶማሊያ ዜና አገልግሎት ሶና ዘግቧል።

ይህ ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ወሳኝ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አቋም ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ሚኒስትሮች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የመከሩ ሲሆን በተለይም በጋራ ፖለቲካዊ እና ደህንነት ጥቅሞች ዙሪያ ያላቸውን ቅንጅት ለማሳደግ የሚረዱ መንገዶችን ማሰሳቸው ተመላክቷል።

ይህ ውይይት በ #ሞቃዲሾ እና በ #ካይሮ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ግንኙነት፣ የጋራ ድጋፍ እና ለቀጠናው መረጋጋት ያላቸውን የጋራ ራዕይ የሚያንፀባርቅ መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል።

ሚኒስትሩ ባድር አብዴላቲ ግብፅ ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ማረጋገጫ፤ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ድንበር መከበር እና የሀገራት ሉዓላዊነት በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ውስጥ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ በሆነበት ወሳኝ ወቅት ላይ የቀረበ ነው።

በተጨማሪም ባለሥልጣናቱ የቀጠናውን የጸጥታ ሁኔታ በጥልቀት የገመገሙ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ምክክሩ የተጠናቀቀው በቀጠናው የሚታዩ አዳዲስ ፈተናዎችን እና ዕድሎችን በጋራ ለመወጣት በቅርበት ዲፕሎማሲያዊ ቅንጅታቸውን ለመቀጠል ቃል በመግባት ነው ሲል ሶና ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...