በሰይፉ የዩትዩብ ቻናል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

Date:

ከየካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰይፉ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል ላይ እየተደረገ በቆየው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ላይ የመጀመሪያው ዙር የገቢ ማሰባሰብ የቀጥታ ስርጭት ግቡን በማሳካት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በይፋ ተጠናቀቀ፡፡

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  በአዲስ አበባ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋውያን መኖሪያና ዘመናዊ ሆስፒታል አጠቃላይ የፊኒሺንግ ስራውን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ከየካቲት 01 ቀን 2017  ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 1 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ በመያዝ በseifu on ebs እና በ Seifu Show ዩቱብ ቻናል ላይ በመጀመር ላለፉት ሶስት ወራት (90 ቀናት) በቆየው ገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን እቅድ በማሳካት አጠቃላይ በገንዘብ እና በአይነት ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በሰይፉ ዩቱዩብ ቻናል የተደረገው የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰብ ግንቦት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል፡፡

ይህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄደበት Seifu on EBS እና Seifu Show ዩቱዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭትና በማስታወቂያ ገቢ የተገኘ ብር 4,032,585.63 ለመቄዶኒያ ገቢ የተደረገ ሲሆን በመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ላለፉት ሶስት ወራት ሲደረግ በቆየው ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ በማመስገን ለዚህ ዝግጅት ዋናውን ሚና ሃላፊነት በመውሰድ የ1 ቢሊየን ብር ግብ እንዲሳካ ላደረገው ለሰይፉ ፋንታሁን ምስጋና በማቅረብ የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን እንዲሁም በመቄዶኒያ በሚገኙ ተረጂዎች በእጅ ጥበብ የተሰራ ጋቢ ለሰይፉ ፋንታሁን እና ለአርቲስት ይገረም ደጀኔ ያለበሱ ሲሆን በአረጋውያኑ ምርቃት በመታጀብም በሰይፉ ፋንታሁን ምስል የተቀረፀ ምስለ ቅርፅ በስጦታ አበርክተዋል፡፡

በዚህ  በሰይፉ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ላለፉት ሶስት ወራት በዘለቀው እና ለተመካቾች በደረሰ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር  ፣ ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የመጡ መምህራን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ፤ ባንኮች እና የሚዲያ ባለሞያዎች መድረኩን በማድመቅ ልግስና በመስጠት እና ለጋሾችን በማበረታታት አብረውን ቆይተዋል። አሁንም በመቄዶንያ ዩቱዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ እንደቀጠለ ነው::

ላለፉት ሶስት ወራት አብራችሁን ስለነበራችሁ ብርታት እና ልግስናችሁ ስላልተለየን እናመሰግናለን !!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...