በአሰሪና ሰራተኛ የህግ ክርክር አዲስ የሰበር ውሳኔ ተላለፈ

Date:



ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ ለአምስት ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር።

ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል።

በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል።


FBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...