በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

Date:

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱን ያስታወቀው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

በሚኒስቴሩ የሕፃናት ድጋፍ አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሀሰን መሐመድ የመንግሥትን ጥናት ጠቅሰው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሚገኙ 132 የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ከ12 ሺሕ አይበልጥም።

እንደ ኃላፊው ገለጻ በ2010 ዓ.ም. በሀገሪቱ የነበሩት የተቋማት ቁጥር 240 ገደማ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን ተቋማቱም ሆኑ የሚያሳድጓቸው ሕፃናት ቁጥር በከፍተኛ መጠን ቀንሷል። ይህ የሆነበት ምክንያትም መንግስት አሳዳጊ የሌላቸው ህጻናት በቤተሰብ ውስጥ እንዲያድጉ የማበረታታት ስራ በመስራቱ ነው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በእነዚህ ተቋማት የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እያገኙ ያሉት ሕፃናት ቁጥር ከ10 እስከ 12 ሺሕ ባለው ክልል ውስጥ እንደሚገኝም ኃላፊው ተናግረዋል።

መንግሥት የሕፃናትን ጉዳይ በበላይነት በመከታተል ባካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት መሠረት፤ ሕፃናቱ በተቋማት ከመቆየት ይልቅ ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉበትና አማራጭ የቤተሰብ እንክብካቤ የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።

ይህም ሕፃናት በተቋም ውስጥ ከማደግ ይልቅ በቤተሰብ ድባብ ውስጥ እንዲያድጉ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ ቢሆንም፤ አሁንም በማሳደጊያ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ የተቀናጀ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በአሰሪና ሰራተኛ የህግ ክርክር አዲስ የሰበር ውሳኔ ተላለፈ

ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት...