በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደረሰ

Date:


በስርቆትና ውድመት የተነሳ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት እና የኃይል ስርቆት ላይ የደረሰበትን ጉዳት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር፤ ባለፉት አራት ወራት በመሰረተ ልማት በተፈጸመ ስርቆት፣ በመኪና አደጋ በደረሰ ውድመት እና በኃይል ስርቆት በድምሩ 114 ሚሊዮን 299 ሺህ 93 ብር የሚገመት ጉዳት በተቋሙ ላይ ደርሷል ብለዋል።

በ17 ትራንስፎርመሮች ላይ በተፈጸመ ስርቆት 23 ሚሊዮን 85 ሺህ 847 ብር ኪሳራ ደርሷል ያሉት ኃላፊው፤ በኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ ኬብል ስርቆት ደግሞ 88 ሚሊዮን 849 ሺህ 858 ብር ጉዳት ደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።

በመኪና ግጭት የደረሰ የመሠረተ ልማት ውድመት ብዛት 15 ሲሆን፣ በብር ሲተመን 18 ሚሊዮን 178 ሺህ 731 ብር ጉዳት ማጋጠሙን አብራርተዋል።

ተቋሙ ባለፉት አራት ወራት 36 ነጥብ 45 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት መፈጸሙን ጠቁመው፤ በዚህም ምክንያት ተቋሙ 13 ሚሊዮን 184 ሺህ 677 ብር አጥቷል ሲሉ አብራርተዋል።

በአጠቃላይ ባለፉት አራት ወራት 107 ጉዳቶች እንደተመዘገቡ ጠቅሰው፤ 10 የወንጀል ክሶች ተመስርተው በፍርድ ሂደት ላይ እንደሚገኙ፣ ቀሪዎቹም በፖሊስ የምርመራ ሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...