በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው ሰደድ እሳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸው ተገለፀ፡፡
በሎስ አንጀለስ በሚገኙት ተራሮች ላይ በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የሰደድ እሳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገድዷል።
እሳቱ በተነሳበት 5 ሰዓት ውስጥ ከ6 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ መስፋፋቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በዚህም የተነሳ ከ 2 ሺህ 700 በላይ ነዋሪዎች መኖሪያቸውን በፍጥነት ለቀው እንዲወጡ የተጠየቁ ሲሆን ለተጨማሪ 14 ሺህ ሰዎች የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።
ካሊፎርኒያ በዚህ ዓመት ከ 4 ሺህ 400 በላይ የእሳት ቃጠሎዎችን ያስተናገደች ሲሆን፣ 89 ሺህ 500 ሄክታር በላይ መሬት ቃጠሎ እንደደረሰበት ፍራንስ 24 ዘግቧል።
ebc
