በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘይሴ ነዋሪዎች ” ካሳለፍነዉ እሁድ ጀምሮ በአከባቢው በአድማ ብተናና የጋሞ ዞን ፖሊስ እየተወሰደ ያለው ተገቢ ያልሆነ የሃይል እርምጃ በርካታ ምስቅልቅሎችን ሲፈጥር ቆይቷል ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 አርሶአደሮች በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ተገድለዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
በአከባቢዉ እየተንቀሳቀሱ ባሉ የታጠቁ የፀጥታ አካላት እየተወሰደ ባለዉ ድብደባና እስር ምክንያት የህብረተሰቡ እቅስቃሴ ተገድቦ መቆየቱን የገለፁት ነዋሪዎቹ ” ‘ ቢቀሳ ‘ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ከብት በረሃብ እንዳይጎዳ አሰማርተዉ የነበሩ 2 አርሶ አደሮችን በጥይት ተመተው ተገድለዋል ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የአከባቢው የሃይማኖት መሪዎች እና ሽማግሌዎች ” እርምጃው ፍፁም ትክክል ያልሆነ ” ሲሉ ገልጸዋል።
ከሰሞኑን የሃይማኖት ተቋማትን ነፃነት የጣሰ ተግባር መፈጸሙን ጠቁመዋል።
” በኤልጎ ሙሉ ወንጌል እና ወዘቄ መካነ ኢየሱስ ቤተክርቲያናት አገልጋዮች ከመድረክ ተጎትተው ተወስደዉ የታሰሩበትና የተደበደቡበት ሁኔታ ነበር። በዚህም ምክንያት በእሁድ ዕለተ የአምልኮ ቀን ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን አልመጡም ” ሲሉ ተናግረዋል።
” የሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ተጥሷል ፣ የጤና ተቀማት የወታደር ከምፕ ሆነዋል፣ ትምህርትና የእርሻ ስራን ጨምሮ አጠቃላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በዘይሴ ኤሊጎ፣ ዘይሴ ዳቢሌ እና ዘይሴ ወዘቄ አከባቢዎች ወዳልተፈለ አቅጣጫ እያመራ ስለሆነ ከዚህ በላይ ቀዉስና ሞት እንዳይከሰት የክልሉ መንግስትና የፌደራል ገለልተኛ አካላት ጣልቃ ገብተዉ ያረጋጉ ” ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች እና ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ ምን አለ ?
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ ከሳምንት በፊት በግዳጅ ላይ ለነበሩ የፀጥታ አባላት ስንቅ ሲወስዱ በነበሩ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ላይ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት አንድ የአድማ ብተና ፖሊስ ተሰውቷል ሲሉ አስታውሰዋል።
” ይህን ጥቃት ያደረሱ ሽፍቶችን ለመያዝ የፀጥታ መዋቅር አካላት ተሰማርተዋል ነገርግን ‘ የሃይል እርምጃ ተወስዶ ሁለት አርሶአደሮች ተገድለዋል ‘ የሚባለው ፍፁም የዉሸት መረጃ ነዉ ” ሲሉ ገልፀዋል።
” ለአከባቢው አለመረጋጋት ዋነኛ ምክንያት የሆኑት ተደብቀዉና በሰሩት ወንጀል የሚፈለጉ አንዳንዶች ደግሞ በሌሉበት የፍርድ ዉሳኔ ተላልፎባቸዉ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ናቸው ” ያሉት አዛዡ ” እነዚህ ግለሰቦች ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የዉሸት መረጃ እያሰራጩ ነዉ ” ብለዋል።
በአከባቢው የሚገኙት የፀጥታ አካላት በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዳይወርድ በሚፈልጉ ፀረ ሰላም ሃይሎች በሰላማዊ ዘጎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ በአከባቢው የሚገኙ ናቸዉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia
