የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ ሆኖ የታየው በቀን ሰራተኞች በተማሪዎች እና በአጠቃላይ በማህበረሰብ ውስጥ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ ከአንድ በመቶ በታች ነው ሲባል ዝቅተኛ ቢመስልም አሁን ባለበት ካልተገታ በድጋሚ ወረርሽኝ የሚሆንበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል፡፡
በተለይም ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ለበሽታ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱ ወረርሽኝ የመሆን እድሉን ሊያሰፋው ይችላል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡
በዚህም ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንዳለ እንደሚገመትም ተናግረዋል፡፡
የስርጭት መጠኑ ከክልል ክልል ይለያያል ያሉት ስራ አስፈፃሚው አዲስ አበባ መጠኑ ከፍተኛ ሆኖ ከሚታይባቸው መካከል ቀዳሚ እንደሆነችም ያስረዳሉ፡፡
ጋምቤላ፣ ሀረሪ፣ ትግራይና አማራ ክልል ከፍተኛ ስርጭት የሚታይባቸው ከተሞች ናቸው ተብሏል።
እድሜአቸው ከ15 እስከ 29 ዓመት ያሉት ወጣቶች እና ሴቶች አዲስ የመያዝ እድላቸው 70 በመቶ ነው ተብሏል፡፡
