በጋዛ ፍርስራሾች መካከል የ54 ጥንዶች ሰርግ ተካሄደ

Date:

የጋዛ ሰርጥ ውስጥ በጦርነት የፈራረሱ ህንጻዎች መሃል በተደረገው  ሰርግ 54 ጥንዶች ተጋቡ።

ይህ ክስተት ለሁለት ዓመታት ከእስራኤል ጋር ከተደረገው አስከፊ ጦርነት በኋላ የታየ ብርቅዬ የተስፋ ብልጭታ ነው ተብሎለታል።

ከጥንዶቹ መሃል አንዷ ኢማን ሃሰን ላዋ በሰጠችው አስተያየት “ምንም እንኳን ያ ሁሉ ነገር ቢፈጠርም፣ ዛሬ አዲስ ሕይወት እንጀምራለን። እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ይህ የጦርነቱ ፍጻሜ ይሆናል” ስትል ተናግራለች።

ሰርጎች የፍልስጤም ባህል ቁልፍ አካል ቢሆኑም፣ በጦርነቱ ወቅት በጋዛ ውስጥ ብርቅ ሆነው ነበር። ምንም እንኳን ሰርጎቹ ቀደም ሲል ይደረጉ እንደነበሩት ደማቅ ሥነ-ሥርዓቶች ባይሆኑም፣ አሁን በእስራኤል እና ፍልስጥኤም መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ምክንያት ባህሉ እንደገና ማንሰራራት ጀምሯል።

በደቡባዊቷ ካን ዩኒስ ከተማ ብዙ ህዝብ የፍልስጤምን ባንዲራ እያውለበለበ ደስታውን ቢገልጽም፣ የሰርግ ስርአቱ በጋዛ እስካሁን ባልጠፋው ቀውስ ምክንያት ድባቡ ተቀዝቅዞ ነበር።

የኢማን ባል የሆነው ሂክመት፣ “እኛም እንደ ሌላው ዓለም ደስተኛ መሆን እንፈልጋለን። ድሮ ቤት፣ ሥራ እና እንደማንኛውም ሰው መሆንን አልም ነበር። ዛሬ ግን ህልሜ የምኖርበት ድንኳን ማግኘት ነው” ብሏል። አክሎም፣ “ሕይወት ወደ መደበኛው ሁኔታ መመለስ ጀምራለች፣ ነገር ግን ተስፋ እንዳደረግነው ዓይነት አይደለም” ሲል ተናግሯል።

ዝግጅቱ ስፖንሰር የተደረገው አል ፋሬስ አል ሻሂም (Al Fares Al Shahim) በተባለው የእርዳታ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ዝግጅቱን ከማካሄዱ በተጨማሪ፣ ጥንዶቹ አብረው ህይወታቸውን እንዲጀምሩ የተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አበርክቷል።(NBC)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...