በናይጄሪያ በተከሰተ ጎርፍ 117 ሰዎች ሞቱ

Date:

በናይጄሪያ በተከሰተ ጎርፍ 117 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣን ገለጹ፡፡

በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት በርካታ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሳቢያ የደሰሱበት አልታወቀም የተባለ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ሰሜን ማእከላዊ ቦታ 3ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶችን በውሃ መዋጣቸው ተሰምቷል፡፡

ሀሙስ እለት የሟቾች ቁጥር 21 የነበረ መሆኑ ሲገለጽ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ እንደሆነም የሀገሪቱን የአደጋ ስጋት ሀላፊ ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ይህ ወቅት በሀገሪቱ የጎርፍ አደጋ የሚበራከትበት ዝናባማ ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ሀገሪቱ ከ3 አመት በፊት በተመሳሳይ በ10 አመታት ውስጥ ከ6 መቶ በላይ ሰዎች እንዲሞቱ ያደረገ እና 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረገ የከፋ የጎርፍ አደጋ ያስተናገደች መሆኑ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...