የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የሚኖራቸው ውይይት “ያለመሳካት ዕድሉ 25 በመቶው ነው” አሉ።
በአልመንዶርፍ ሪቻርድሰን የጦር ሰፈር ፣አንከሬጅ አላስካ ውስጥ ዛሬ የሚገናኙት መሪዎቹ በርካታ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተለይም የዩክሬኑን ጦርነት መቋጨት የፑቲንና ትራምፕ ቁልፉ አጀንዳቸው ነው።
ከፎክስ ኒውስ ሬዲዮ ጋር ትራምፕ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ‘ውይይቱ አይሳካ ይሆን የሚል ጥያቄ ሲነሳላቸው’ “አዎ!ያለመሳካት ዕድሉ 25 በመቶ ነው።” ሲሉ መልሰዋል።
ስብሰባው ሁለተኛውን ዙር ስብሰባ የሚያመቻች መሆኑን ያመኑበት ትራምፕ የተለያዩ አስተያየቶችን አስቀድመው በመስጠት ላይ ተጠምደዋል።
ውይይቱ ሌላ ዙር ድርድርን በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ መካከል ለመፍጠር በር ይከፍታል የሚል አቋም ዋይት ሀውስ ያራምዳል።
መሪዎች በግዛት አሳልፎ መስጥትና አስቸኳይ ተኩስ አቁም መርህ ውስጥ ሆነው ይደራደራሉ።
ምናልባትም ፑቲንና ትራምፕ ከተስማሙ ወዲያውኑ ከዘለንስኪ ጋርም ውይይቱ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው ።
.
