በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የልጆች መጻሕፍት በኢትዮጵያ በተሰኘ ርዕስ የልምምድ ልውውጥና ሙያዊ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ሙያዊ ውይይቱ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 10 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ይካሄዳል።
የዕለቱ ተጋባዥ ከ120 በላይ መጻሕፍትን ለሕትመት ያበቃው የልጆች መጽሐፍ ደራሲ፣ ተርጓሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መምህር ዓለም እሸቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ አድርጓል፡፡
በዕለቱ የሥነ ጥበባት ማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት በኢትዮጵያ የልጆች መጻሕፍት ታሪክና ተግዳሮት ዙሪያ የመነሻ ጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡
ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ሲሆን በዕለቱ በዘርፉ የተሰማሩ የልጆች መጽሐፍ ደራሲያንና ባለሙያዎችና ይሳተፋሉ፡፡
