የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር የሚተገበሩ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ መመሪያ አስተላለፈ።
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ «የሙያና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜ ጋር በተመጣጠነ መልኩ ይሰጣል» በሚለው አቅጣጫ መሠረት፣ በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በ12 የሙያ ዓይነቶች ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሚተገበሩት 11 ተጨማሪ የሙያ ዓይነቶች የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ-ትምህርቶችን፣ እንዲሁም የ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችንና የመምህራን መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ለዚሁ ትግበራ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፦
👉ዝርዝር ዕቅድና በጀት በመያዝ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤትና በተማሪዎች ደረጃ እንዲያስመርጡ፣
👉የሙያ መምህራንን እንዲቀጥሩና እንዲያሰለጥኑ፣
👉የመማሪያና ማስተማሪያ ግብዓቶችን እንዲያሟሉ፣
የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠንና የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የአዲሶቹ 11 የሙያ ዓይነቶች ዝርዝር፦
👉ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ
👉አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
👉አልባሳት ቴክኖሎጂ
👉ሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
ቧንቧ ሥራ
👉ሶፍትዌር ማበልጸግ
👉ሰብል አመራረት
👉ጤና ክብካቤ አገልግሎት
👉ሆቴል አገልግሎት
👉ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
👉ምግብ ዝግጅት
