የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዎቹ ቀናት ለመገናኘት መስማማታቸውን የክሬምሊን ረዳት ተናግረዋል።ትራምፕ ከሩሲያ እና የዩክሬን መሪዎች ጋር በአካል ተገናኝተው በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም “በቅርቡ” ለመገናኘት ጥሩ እድል አለ ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ረቡዕ ምሽት በዋይት ሀውስ መግለጫ ላይ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና ፑቲን የሶስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ መስማማታቸውን ለቀረበላቸው ጥያቄ ትራምፕ “በጣም ጥሩ ተስፋ” እንዳለ ቢገልጹም አላብራሩትም፡፡
ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት እንድታደርግ ወይም ተጨማሪ ማዕቀብ ሊጣልባት የሚችል ሲሆን ትራምፕ ቀነ-ገደቡ ከመጠናጠቀቁ በፊት እንድትስማማ ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡
ትራምፕ የሰጡት አስተያየት በሞስኮ በልዑካቸው ስቲቭ ዊትኮፍ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የተደረገ ውይይትን ተከትሎ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት “በጣም ውጤታማ ነበር” ሲሉ ገልጸውታል።
የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ቀደም ብሎ እንደዘገበው ትራምፕ በሚቀጥለው ሳምንት ከፑቲን ጋር በአካል ተገናኝተው እንደሚመክሩ ይጠበቃል፣ በቀጣይም ከዘለንስኪ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል ጽፏል።
ዘለንሲኪ በበኩሉላቸዉ ስለ ዊትኮፍ ጉብኝት ከትራምፕ ጋር መነጋገራቸውን ተናግረዋል።ዜለንስኪ ሩሲያ ገንዘብ ማጣት ከጀመረች ብቻ ወደ ሰላም ለመምጣት ከፍተኛ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጸዋል።ሐሙስ እለት የዩክሬን መሪ በሶስትዮሽ መሪዎች መካከል ለሚደረገው ስብሰባ ድጋፉቸዉን አሳይተዋል፡፡
