በካሪቢያን ባህር የምትገኘው እና በትንሽ የህዝብ ቁጥር የምትታወቀው ኩራሳኦ ለ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች።
ኩራሳኦ ወደዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ የደረሰችው ወሳኝ በተባለው የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ ከጠንካራዋ ጃማይካ ጋር 0-0 በሆነ ውጤት በመለያየት ነው።
ይህ ውጤት በምድብ “2” አንደኛ ሆና እንድታጠናቅቅ እና በቀጥታ ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የዓለም ዋንጫ እንድታመራ አስችሏታል።
185,000 የሚጠጋ የህዝብ ቁጥር ያላት ኩራሳኦ ለአለም ዋንጫ ማለፍ የቻለች ትንሿ ሀገር በመሆን አዲስ ታሪክም መጻፍ ችላለች።
