አሐዱ ባንክ የኢንሹራንስ ክፍያን በተመለከተ  የሁለትዮሽ ስምምነት አደረገ!

Date:

አሐዱ:ባንክ በተነሣበት ከብዙዎች ለብዙዎች መርሕ ለብዙዎች ለመድረስ አጠናክሮ በመቀጠል ከኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ  ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት ሐመር አዳራሽ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም ስምምነት አደረገ::

የኢንሹራንስ ደንበኞች ለመኪናቸው የሚከፍሉትን ዓመታዊ የአረቦን ክፍያ 22% ብቻ  በአሐዱ፡ባንክ በኩል ከቆጠቡ ባንኩ ፋይናንስ በማድረግ  ዓመታዊ የኢንሹራንስ  ክፍያቸውን እንደሚከፍልላቸው እና በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን የአሐዱ:ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገብሩ በአፅንኦት ተናግረዋል::

የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽመልስ ገብረ ጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ ከተለመደው አሠራር ወጣ ብለን ውጤት እና እድገት ላይ በማተኮር ተባብረን በመሥራት የጋራ ደንበኞቻችንን ለማገልገል አጋርነታችን እጅጉን ወሳኝ ነው በማለት ገልጸዋል::

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...