አሜሪካ ለሶማሊያው የምትሰጠውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ ልታቋርጥ ነው

Date:

በሶማሊያ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን ይዞ ለመሰማራት የታቀደው አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና ማረጋጊያ ተልዕኮ (AUSSOM) በአሜሪካ ምክንያት መስተጓጎል ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

አሜሪካ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የሚያደርገውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ ልታቋርጥ በመወሰኗ ምክንያት የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበት ሮይተርስ የዲፕሎማሲ ሰነዶችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

በተመድ የሶማሊያ ድጋፍ ሰጪ ቢሮ (UNSOS) በኩል ለሚቀርቡት እንደ ምግብ፣ ነዳጅ፣ ሕክምና እና ማመላለሻ ላሉ የሎጂስቲክስ አቅርቦቶች የአሜሪካ ድጋፍ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው።

​ይሁን እንጂ ዋሽንግተን ለአፍሪካ ኅብረት በላከችው ዲፕሎማሲያዊ ማስታወሻ፥ ከ2026 ማብቂያ በኋላ ይህንን የሎጂስቲክስ ድጋፍ እንደማትደግፍ ያስታወቀች ያስታወቀችው።

አሜሪካ ለዚህ ውሳኔ በምክንያትነት የጠቀሰችው የሶማሊያ መንግሥት የውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ እንዲሁም በዚህ ሁሉ ዓመታት የዓለም አቀፍ እርዳታ አልሸባብን ማሸነፍና የሀገሪቱን የጸጥታ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ መረከብ ባለመቻሉ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ዋሽንግተን ባለፉት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ብታፈስም የሚጠበቀውን ውጤት አለማግኘቷም ለውሳኔው ምክንያት መሆኑ ነው የገለጸው።

​ይህ የአሜሪካ ውሳኔ ሌላ አማራጭ ድጋፍ ካልተገኘ ተልዕኮው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ሊያደርግ እንደሚችል የአፍሪካ ኅብረት እና ዲፕሎማቶች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ይህም በሶማሊያ ውስጥ የአልሸባብ ጥቃቶች እንደገና እንዲያገረሹ እና የሀገሪቱ መንግሥት ይበልጥ እንዲዳከም በር የሚከፍት በመሆኑ በምሥራቅ አፍሪካ የጸጥታ መዋቅር ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነ ነው።

​Credit: Reuters

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሁቲዎች በሳዑዲ አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

የየመን ሁቲ አማጺያን የሳዑዲ አረቢያን አውሮፕላን ማረፊያዎች እና ሌሎችም...

“የድንቁርና” እና “የታሪክ ፍልሠትን” የሚያስከትል ድርጊት ነው

የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዓለማቀፍ ቅርስ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት፣...

በመቐለ ከተማ በወጣቶች ላይ “የግዳጅ አፈሳ” ተጀምሯል

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የጸጥታ ኃይሎች በወጣቶች ላይ...

በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ መሸጫ ክልከላ ርቀት ወደ 500 ሜትር ከፍ ተደረገ

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ...