አሜሪካ ከጃፓን ጋር የንግድ ስምምነት አደረገች

Date:

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሺንግተን ከጃፓን እና ፊሊፒንስ ጋር ትልቅ የንግድ ስምምነት መድረሷን አስታውቀዋል።

የንግድ ስምምነቱ የአሜሪካ ትልቋ የንግድ አጋር ለሆነችው ጃፓንም ሆነ አሜሪካ
ትልቅ የሚባል ሲሆን፥ ከዚህ በፊት የነበረውን የቀረጥ መጠን መቀነስ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በስምምነቱ መሰረት 25 በመቶ የነበረውና ተሽከርካሪን ጨምሮ በተለያዩ ሸቀጦችላይ ተጥሎ የነበረው ቀረጥ ወደ 15 በመቶ እንዲወርድ ያደርጋል መባሉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ስምምነቱን የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺጌሪ ኢሺባ አድንቀውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምምነቱ በአግባቡ ተግባራዊ ከተደረገ ሃገራቸው በአሜሪካ
የ550 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ታደርጋለች ብለዋል።

ስምምነቱን ተከትሎ ተቀዛቅዞ የነበረው የጃፓን የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎችየአክሲዮን ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...