አሜሪካ የኢራን ወደቦችን ለመዝጋት ማቀዷን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

Date:



አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ መርከቦችን ለማገድ የባሕር ላይ ከበባ እንደምታደርግ ማስታወቋን ተከትሎ፤ ሰኞ ሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. በማለዳው የገበያ ግብይት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

አልጀዚራ እንደዘገበው፤ የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ (US crude oil) ዋጋ 8 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 104.24 ዶላር ደርሷል።

የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት (Brent) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በ7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 102.29 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

ዓለማቀፉ ግዙፍ የኢነርጂ ገበያ ተንታኝ ኦኒክስን (Onyx) ዋቢ በማድረግ ብሉምበርግ እንደዘገበው ደግሞ፤ አሜሪካ የባሕር ላይ ከበባውን የምትቀጥል ከሆነ ዓለማቀፍ የነዳጅ ዋጋ እስከ 150 ዶላር ሊያሻቅብ ይችላል።

የአሜሪካና የእስራኤል ጥቃት በኢራን ላይ በየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከመጀመሩ በፊት፤ በአንድ በርሜል 70 ዶላር ገደማ ይሸጥ የነበረው የብሬንት ነዳጅ ዋጋ፤ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ፤ ከፍተኛ መዋዠቅ የታየበት ሲሆን፤ በአንድ በርሜል እስከ 119 ዶላር ደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም. አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ንግግር ከማድረጋቸው በፊት፤ ለሰኔ ወር የሚቀርብ የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በ0.8 በመቶ ቀንሶ በበርሜል 95.20 ዶላር ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...