አምስት የምርጫ ጣቢያዎችን መታዘብ ግዴታ መሆኑን ተናገረ

Date:

የኢትዩጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የሚመለምላቸዉ 2 ሺህ ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎች አምስት የምርጫ ጣቢያዎችን መታዘብ ግዴታ መሆኑን ተናገረ

ህብረት ለምርጫ በአሁኑ ወቅት 1 መቶ 90 የሚደረሱ በሀገሪቱ በዲሞክራሲ ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የያዘ ነዉ።

እየተቃረበ ባለዉ 7 ተኛዉ ብሄራዊ ምርጫ በቅድመ ምርጫ ታዛቢነት 5 መቶ 90 የሚሆኑ ታዛቢዎች ማሰማራቱን ሰምተናል።

ይህን ያሉት የህብረት ለምርጫ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አበራ ሃይለማርያም ታዛቢዎች የምርጫ ክርክርን÷ ዘመቻዎች በአጠቃላይ የሲቪክ ምህዳሩን የሚያዩ መሆናቸው ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ በድምፅ መስጫ ቀንም ሂደቱን የሚከታተሉ ተቀማጭ እና ተንቀሳቃሽ 5 ሺህ ታዛቢዎች ይመለመላሉ ብለዋል።

ሁኔታዎች እስከተመቻቹ ድረስ ታዛቢዎቹ በመላዉ ሀገሪቱ የሚሰማሩ ናቸዉ የተባለ ሲሆን 3 ሺህ ያህሉ ተቀማጭ ታዛቢዎች ቀሪዎቹን ደግም ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎች ናቸዉ ተብሏል።

አቶ አበራ እያንዳንዱን ተንቀሳቃሽ ታዛቢ አምስት የምርጫ ጣቢያዎችን የመታዘብ ግዴታ የሚኖርበት መሆኑን አብራርተዋል።

በ አምስተኛዉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በተደረጉ ዉይይቶች አንዱ የሆነዉ በምርጫ ሂደት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የተመለከተው ይገኝበታል።

አቶ አበራ ሀይለማርያም ህብረቱ በ7 ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ 28.5 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎችን የመታዘብ አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

በድህረ ምርጫ ወቅትም በየምርጫ ጣቢያዎች ዉጤቶች መለጠፋቸዉን  ÷ የህዝቡ ስሜት ምን እንደሚመስል የሚገመግሙ መሆኑን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...