ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የጣልያን አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን አነጋገሩ

Date:


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ አዲሱ የኢጣልያ  አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ  በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።።                                                 በውይይቱ ወቅት ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፣ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።                                  ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት መሆኗን ጠቅሰው፣ ከጣልያን ጋር ያሏት ታሪካዊ ግንኙነቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።                                                                                  ቅዱስነታቸው በውይይቱ ወቅት ባስተላለፉት ጥልቅ የሰላም እና የሰብአዊነት መልዕክት፤ ዓለማችን ማንኛውም ፍጡር የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖርበት በእኩልነት፣ በመከባበር እና በሰብአዊነት አስተሳሰብ ሊኖርባት የተሰጠች መሆኗን ገልጸዋል።          በመሆኑም ሕይወታችንን በሰላማዊ መንገድ መምራት እንደሚገባ ጠቅሰው፤ “እኛ የሃይማኖት  አባቶች ሁሌም በትጋት በሀገራችን ብሎም በመላው ዓለም ሰላምና ፍቅር እንዲሰፍን እንጸልያለን” ብለዋል።                                                                  
አምባሳደ ሴም ፋብሪዚ ከቆይታቸው በኋላ ለብዙኃን መገናኛ ድርጅት (#EOTCTV) ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር መወያየታቸው እንዳስደሰታቸው ጠቁመው፣ ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥንታዊና ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንገልጸዋል።                                                                                   አምባሳደሩ አክለውም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ ማኅበራዊ ትስስር እና የታሪክ ግንባታ ውስጥ ያላትን ሚና ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጡት ተናግረዋል።   

   እንዲሁም አምባሳደሩ   ይህንን የቆየ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጣሊያን በሰላምና በልማት ዘርፎች ላይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ጠቁመዋል።                                                              

በተለይም ከሀገራቸው መንግሥት ጋር በመሆን በዘላቂ ሰላም ዙሪያ ይበልጥ እንደሚሠሩ አመላክተዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...