ለአንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ገቢ ማሰባሰቢያ ሊካሄድ ነው

Date:

ለአንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም የመነኮሳት ማረፊያ ሁለት የባለ 2B+G+5 ህንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ ሊካሄድ መሆኑን የገዳሙ አባቶች በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል::

ለዚህም የመነኮሳት ማረፊያ ሁለት የባለ 2B+G+5 ህንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት ከመጋቢት 11 እስከ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ሌሊቶች የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀገብር ይካኼዳል ተብሏል::

ቀጥታ ሥርጭቱም ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ከመጋቢት 11 እሰከ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ሌሊቶች ይካኼዳል፡፡

በመሆኑም የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በሀገር ውጭ እና በውስጥ ያሉ የተዋሕዶ ልጆችና ወዳጆች ለሐምሳ ሰው እንዲያደርሱ፤ ብሎም በተጠቀሱት ቀናት በሚዲያዎች በቀጥታ ሥርጭት እየተከታተሉ በገንዘብ እና በቁሳቁስ በማገዝ ከጎናችን እንድትሆኑ ሲሉ የገዳሙ አባቶች ጥሪ አቅርበዋል

በመግለጫው እንደተጠቆመው የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያት ገዳሟ 1200 ካሬ ላይ ያረፈ ባለ ሁለት ቤዝመንት እና ባለ ስድስት ወለል ሁለገብ ሕንፃ እየገነባች በመሆኑ ነው እንዲሁም ይኽ ሕንፃ 640,000,000.00 /ስድስት መቶ አርባ ሚሊዬን ብር የሚጨርስ ስለሆነ እስካሁን 135,000,000.00/አንድ መቶ ሰላሣ አምስት ሚሊዬን ብር ከአውደ ምሕረት እና ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች ተሰብስቦ /20% ሃያ ፐርሰንት ሥራው ተሠርቶ በገንዘብ እጥረት በመቆሙ ነው

ሕንፃውን መገንባት ያስፈለገበት ምክንያትም የክርስትና ማጥመቂያ አዳራሽ፣ለምእመናን አገልግሎት የሚሰጥ ለሠርግ፣ ለስብሰባ፣ ለልዩ ልዩ ተግባራት የሚውል አዳራሽ፣ለአባቶች ማረፊያ፤ለገዳሙ ለልዩ ልዩ ጽ/ቤቶች በተጨማሪ ለፉካ እና መሰል ጉዳዮች እንደሆነ ተገልጿል

እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ሥር ከሚገኙ ጥንታውያን እና ታሪካውያን ገዳማት አንዷ እና ዋነኛዋ ስትሆን ከአንድ መቶ አርባ በላይ አገልጋዮች ዓመቱን ሙሉ ያለ እረፍት የሚያገለግሏት መቅደስ ናት፡፡

✅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000003780779
✅ በአቢሲኒያ ባንክ 9841011002322017
✅ በኦሮሚያ ባንክ 0088911720301

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...