በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሰፍራዎች ከ24 ሺህ በላይ አዳዲስ ህንፃዎች በግንባታ ላይ ናቸው ተባለ። ይህን ያለን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ነው ።
ግንባታዎቹ ለተለያዩ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ለንግድ ማዕከላት የሚውሉ ሲሆኑ ለከተማ አጠቃላይ ዕድገት፣ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ጥቅም እንዳላቸው ተቋሙ ገልጾልናል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአዲስ አበባ የህንፃዎች ግንባታ የደህንነት አጠባበቅ ከፍተኛ ክፍተት ያለበት እንደሆነ መገምገሙን ሰምተናል።
ይህን መልክ ለማስያዝ የግንባታ የደህንነት መመሪያዎች በተገቢው መልኩ እንዲተገበሩ አሳስቧል ።
ቀደም ብሎም በጥቅሉ በከተማዋ የሚገኙ የህንፃ ባለቤቶች ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 24 ሺህ ህንፃዎችን ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ተደረገዋል ።
በዚህም የከተማዋን ድረጃ ከፍ ከማድረጋቸውም ባሻገር ለበርካቶች የስራ እድልን መፍጠራቸወን ተገልጿል ።
