ኢራን ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን ሦስት ሰዎች ሰቀለች

Date:

ኢራን ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር ተብለው የተከሰሱ ሦስት ሰዎችን በስቅላት መቅጣቷን የአገሪቱ የፍትሕ ተቋማት የዜና ምንጭ አስታወቀ።

‘ሚዛን’ የተባለው የኢራን ፍትሕ ተቋማት የዜና ወኪል እንደዘገበው በስቅላት የተቀጡት ግለሰቦች በተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ ግድያዎችን ለመፈጸም የሚያስችሉ “ቁሳቁሶችን” በድብቅ ለማስገባት በመሞከር ተከስሰዋል።

የዜና ወኪሉ በስቅላት የተቀጡት ሰዎች ስምን የዘረዘረ ሲሆን፣ እነሱም ኢድሪስ አሊ፣ አዛድ ሾጃይ እና ራሱል አሕማድ ራሱል ናቸው።

ግለሰቦቹ እስራኤልን “የሚተባበር ድርጊት” በመፈጸም ተይዘው ነው ለስቅላት ላበቃቸው የፍርድ ሂደት የበቁት።

እስራኤል በኢራን ላይ የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎ ለ12 ቀናት በቆየው የሁለቱ አገራት ግጭት ወቅት የእስራኤል የሰላዮች እና ተባባሪዎቻቸው በኢራን ውስጥ የተለያዩ ተግባራት መፈጸማቸው ሲነገር ቆይቷል።

ይህንንም ተከትሎ ኢራን ለቀናት በዘለቀው ግጭት ወቅት ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተከሰሱ 700 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለኢራን መንግሥት ቅርበት ያለው ‘ኑር ኒውስ’ የተባለው መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...