ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ250 ሚ. ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ ለከተማ ማህበረሰብና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

የገንዘብ ሚኒስቴር እና ዓለም ባንክ የከተማ ምርታማ ሴፍቲኔትና ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን ለማስፈጸም የሚውል የ250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰው እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ፈርመውታል።

ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ የሚኖሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸዉን የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶችን በሥራ ገበያው ውስጥ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረዉን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...