ቤተክርስቲያኗ በፒያሳና አራት ኪሎ ሁለት ሕንጻዎች ልትገነባ ነው

Date:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በፒያሳና አራት ኪሎ ለምታስገነባቸው ሕንጻዎች የሳይት ርክክብ ተደረገ።

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በፒያሳና በአራት ኪሎ የሚገነቡትን የቤተክርስቲያኗን ሕንጻዎች በጨረታ ላሸነፉ ኮንትራክተሮች ሳይተቶቹን አስረክዋል።

በዛሬው ዕለት ርክክብ የተደረገላቸው ሳይቶች ፒያሳ አካባቢ የሚገነባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዝክረ ቅዱሳን ህንጻ G+7አንዱ ሲሆን የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ምንሀር ኮንስትራክሽን የተባለው ሕንጻ ተቋራጭ አሸንፎ ሳይቱን የተረከበ ሲሆን አራት ኪሎ አካባቢ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀርባ ባለው ስድስት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሕንጻ አበው በሚል ስያሜ ለሚገነባው B3+G+12 ሁለገብ ሕንጻ ደግሞ አተም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተባለው ኮንትራክተር አሸናፊ በመሆን ሳይቱን ተረክቧል።

በሁለቱ ቦታዎች የሚገነቡት ሕንጻዎች ማለትም በአራት ኪሎ አካባቢ የሚገነባው ሕንጻ በሰላሳ ወራት፣ ፒያሳ አካባቢ የሚገነባው ሕንጻ ደግሞ በሃያ ወራት ውውጥ ተገንብተው የሚጠናቀቁና አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሆናቸው ታውቋል።

በሳይት ርክክቡ ወቅት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት፤ “ቤተክርስቲያን የምታስገነባቸውን ሕንጻዎች ለመሥራት አሸናፊ በመሆናችሁ እድለኞች ናችሁ፤ የግንባታ ሥራውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በጥራትና በፍጥነት በመሥራት እንድታስረክቡ አደራ እንላለን” ብለዋል።

(የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...