ኢጋድ ሱዳን በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ ተቀበለ

Date:

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሱዳን ሪፐብሊክ በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ በደስታ እንደሚቀበል አስታወቀ።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የሱዳን ወደ ኢጋድ የመመለስ ውሳኔ ለቀጣናዊ አንድነት፣ ትብብር እና የጋራ ርምጃ አዲስ ቁርጠኝነትን ያሳያል።

የኢጋድ መስራች አባል የሆነችው ሱዳን ወደ ድርጅቱ መመለሷ የተቋሙ የጋራ ቀጣናዊ ተግዳሮቶችን የመፍታት ችሎታን እንደሚያሳድግ አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ላደረጉት ጥረት አመስግነው÷ በውይይት እና የጋራ መግባባትን በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።

ድርጅቱ ሀገሪቱ አሁን ላይ ለገጠማት ተግዳሮቶች ሰላማዊ መፍትሄዎችን በመደገፍ እና ቀጣናዊ መረጋጋትንና ልማትን ለማሳደግ በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...