ከትግራይ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች ጥር 30/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ ትግራይና ዓፋር ደንበር ድረስ ተጉዘው ነበር።
የሃይማኖት አባቶቹ ቦታው ላይ ሆነው በሰጡት መግለጫ ፤ የጉዞአቸው ዋና ዓላማ በትግራይ ኃይል እና ‘ ሰራዊት ሰላም ትግራይ ሓራ መሬት ‘ ብሎ ራሱን በሚጠራውን ታጣቂ ኃይል መካከል ሰሞኑን ውግያ መካሄዱን ተከትሎ ዘላቂ እርቅ እንዲወርድ ለመለመንና ለመገሰፅ ነበር።
የሃይማኖት አባቶቹ የታጣቂ ኃይል አመራሮቹም አግኝተው ለማነጋገር ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ ቦታው ላይ በመሆን ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
የሀይማኖት አባቶቹ ተስፋ ባለመቁረጥ የእርቅ ጥረታቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
‘ ሰራዊት ሰላም ትግራይ ሓራ መሬት ‘ ብሎ ራሱን የሚጠራውን ታጣቂ ኃይል ይህንን መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስለ እርቅ ሂደቱና ጥረቱ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።
የታጣቂ ኃይሉ ከፍተኛ አመራሮች በግላቸው የማህበራዊ ትስስር ሚድያ ገፅ ” የዘገየ ለአንዱ ወገን ያደላ ፤ ‘ እጃችሁን ስጡ ‘ለማለት ያለመ ‘ በማለት በማጣጣል ፅፈዋል።
” ራሱን ከኮር በላይ አመራር ብሎ የሚጠራው ከህወሓት አመራር የተጣበቀ ኃይል አማሮን ነው በረሀ ለመውጣትና ጠብመንጃ ለማንገብ የተገደድነው የሃይማኖት አባቶቹ እኛን ሳይሆን መቐለ የሚገኘውን ይህንን ኃይል ነው ተው ብለው መለመንና መገሰፅ ያለባቸው ” በማለት ፅፈዋል።
የትግራይ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ የሃይማኖት አባቶች የእርቅና የተግሳፅ ጥረት ሙከራ አለመሳካት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ፤ የሃይማኖት አባቶች ጥረትና ድካም በማድነቅና በሚገጥሟቸው እንቅፋቶች ሳይደናቀፉ ያለመታከት የጀመሩት የሰላም ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ በመማፀን ” የእርቅ ጅማሬው እንዲሳካ ግማሽ መንገድ ተጉዘን እንደግፋለን ” ብሏል።
tikvahethiopia
