በሊባኖስ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጊዚያዊ ሃይል እንዳስታወቀው ማክሰኞ ማለዳ ላይ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ተመድ ቦታ እንዳይገቡ የሚከለክሉትን መንገዶች ለማፅዳት ከሚሰሩት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች አጠገብ አራት ቦምቦችን መጣላቸው አስታውቋል።
ባለፈው ህዳር ወር የጦርነት ስምምነቱ ከፈረሰ በኋላ ይህ በ ተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራተኛ እና ንብረቶች ላይ ከደረሱት በጣም ከባድ ጥቃቶች አንዱ ነው ሲል ተቋሙ ዛሬ ረቡዕ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
“ከተጣሉት ቦምቦች መካከል አንደለ በ20 ሜትር ርቀት ሌሎች ሶስት ደግሖ በ 100 ሜትሮች ርቀት ላይ በነበሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች እና ተሽከርካሪዎች ጉዳት አድርሰዋል” ተብሏል።
እ.ኤ.አ. በህዳር 2024 ከሂዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል በሊባኖስ ላይ በየቀኑ ጥቃቶችን እየፈፀመች መሆኗ ይነገራል።
