እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ጣቢያና እስር ቤት ላይ አዲስ ጥቃት ፈፀመች

Date:

እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ቀጥለዋል። ዛሬ [ሰኞ] እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ፈፅማለች። ለመሆኑ እስካሁን ስለተፈጠረው ምን እናውቃለን?

የኒውክሌር ጣቢያ ላይ የተፈፀመ ጥቃት፡ እስራኤል ለኢራን የኒውክሌር ዓላማ ወሳኝ በሆነው እና ከምድር በታች በሚገኘው የፎርዶ የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈፀሟን አሳውቃለች። የእስራኤል ጦር ጥቃቱን የሰነዘረው ወደ ጣቢያው የሚወስዱ መንገዶችን ለማውደም ነው ብሏል።

ኤቭን እስር ቤት፡ በመዲናዋ ቴህራን የሚገኘው ኤቭን እስር ቤት በተፈፀመበት ጥቃት መውደሙን የፍትህ አካላት ተናግረዋል። የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ፣ እስር ቤቱ የኢራን አገዛዝ “ጠላቶችን” የያዘ ነው ብለዋል።

በሌሎች ቦታዎች የተፈፀሙ ጥቃቶች፡ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ካትዝ የኢራን መንግሥት ብዙ ጊዜ ተቃውሞዎችን ለማፈን የሚጠቀምባቸው ሚሊሻዎች ዋና መሥሪያ ቤት ዒላማ መደረጉን ገልጸዋል። በኢራን የሚገኙ ነዋሪዎችም የኃይል መቋረጥ እንዳጋጠመ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በእስራኤል፡ ኢራንም በእስራኤል ላይ በርካታ የአየር ድብደባዎችን ፈፅማለች። እስካሁን በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት ባለሥልጣናቱ አልገለጹም፤ ነገር ግን በደቡባዊ የእስራኤል ክፍል 8 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች የኃይል መቋረጥ እንዳጋጠማቸው አሳውቀዋል።

ኃይለ ቃላት፡ እስራኤል “ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ” ኃይሏ ኢራንን እየደበደበች እንደሆነ የገለጸች ሲሆን፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕም ትናንት የአገዛዝ ለውጥ ሊፈጠር የሚችልበትን ዕድል እንዳለ አንስተው ነበር።

ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው “አሁን ያለው የኢራን አገዛዝ ኢራንን በድጋሚ ታላቅ ማድረግ ካልቻለ የአገዛዝ ለውጥ የማይኖረው ለምንድን ነው?” ሲሉ ጽፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...