“እኛን ለማጥፋት የሚፈልግን ኃይል አሸንፈን ሀገራችንን መገንባት ጀምረናል”– ቤንያሚን ኔታንያሁ

Date:

እኛን ለማጥፋት የሚፈልግን ኃይል አሸንፈናል፤ እናም አሁን ከጦርነቱ በኋላ እንደገና ሀገራችንን የመገንባት ስራ ጀምረናል  ሲሉ ቤንያሚን ኔታንያሁ ገለጹ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እኛን ለማጥፋት በፈለገችው የክፋት ዘንግ ላይ ትልቅ ስኬት እና ታላቅ ድል አድርጋለች ሲሉ በቅርቡ ከኢራን ጋር የገጠማትን ግጭት አስመልክተው በመግለጫቸው ተናግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ኔታንያሁ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ ያለውን የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ መጀመሯን አረጋግጣለሁ ብለዋል።

የእስራኤል ጦር የበላይነቱን በማሳየቱ የህልውና ስጋቶችን አስወግዷል ሲሉም ገልጸዋል።

ኔታንያሁ አክለውም “ሊያጠፉን ከሚፈልጉ  ኃይሎች ጋር ጦርነት ገጥመን ከዛም የበለጠ ተጠናክረን ተባብረን  ተወጥተነዋል” ብለዋል።

በሚቀጥለው ምዕራፍ እስራኤል ከመልሶ ግንባታ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች  ከፊቷ በማስወገድ ሀገራችንን መገንባት አለብን ሲሉ ለህዝባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...