እጽ አዘዋዋሪዎችን እየደመሰስኩ ነው – አሜሪካ

Date:

አሜሪካ በቬንዙዌላ የባህር ዳርቻ ዕፅ አዘዋዋሪ  ጀልባ ላይ በወሰደችው እርምጃ 4 ሰዎች መግደሏን አሳወቀች።

የአሜሪካ ጦር ትላንት አርብ በቬኔዙዌላ የባህር ዳርቻ ላይ ወደ አሜሪካ አደንዛዥ እፅ ሲታጓጉዝ የነበረ ጀልባን መምታቱን  የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት ተናግረዋል።

በእርምጃው አራት ”ናርኮ” የተሰኙ የአሸባሪ ቡድን አባላት መገደላቸውን የፔንታጎን ዋና አዛዥ ተናግረዋል።

በካሪቢያን አካባቢ አደንዛዥ ዕፅ ያዘዋውራሉ በተባሉ መርከቦች ላይ የሚደረገው ዘመቻ ፥ ፕሬዝደንት ትረምፕ የህግ አውጭዎች ይፋዊ ማስታወሻ ላይ አሜሪካ አሁን ከአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች ጋር ጦርነት ውስጥ መሆኗን እና ከአዘዋዋሪዎቹ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ህገወጦች መሆናቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

በዚህም አሜሪካ አደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎችን ያለመ የጥቃት ዘመቻ የቀጠለች ሲሆን፥ ከሳምንታት በፊትም የአሜሪካ  ኤፍ-35  ስውር ተዋጊ ጀቶች በቬኔዙዌላ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ቡድን ሰፈሮች ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...