ዛሬ ማለዳ አሜሪካ ሦስት የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን በቦምብ መደብደቧን ተናግራለች። እነዚህም ፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን ናቸው።
የእስራኤል መከላከያ በእነዚህ ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት መጠን እየገመገመ መሆኑን ገልጿል።
በአሜሪካ ጥቃት ዒላማ የነበረው ፎርዶ ከዋና ከተማዋ ቴህራን በስተደቡብ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ከመሬት በታች በጥልቅ ዋሻዎች ውስጥ የተሸሸገ ነው።
ፎርዶከምድር በታች ያለው ጥልቀት እስራኤል ባሏት የጦር መሳሪያዎች ለመድረስ አስቸጋሪ ነው።
ፎርዶንለማውደም የሚያስችል ጠንካራ እና ትልቅ “ምሽግ ደርማሽ” ቦምብ ያላት ደግሞ አሜሪካ ብቻ ናት።
አሜሪካያላት ቦምብ ጂቢዩ-57 ማሲቭ ኦርዲናንስ ፔኔትሬተር (ኤምኦፒ) ይባላል።
ክብደቱ 13,000 ኪ.ግ ሲሆን ባለሙያዎች ከመፈንዳቱ በፊት ወደ 18 ሜትር ኮንክሪት ወይም 61 ሜትር መሬት ውስጥ ዘልቆ መግባት ይችላል ይላሉ።
የፎርዶዋሻዎች ከመሬት በታች ከ 80 እስከ 90 ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኙ ይታመናል።
ስለዚህምኤምኦፒ ውጤታማ በሆነ መልኩ ያወድመዋል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር አይቻልም።
ነገርግን ተቋሙን ለማውደም ሊቀርብ የሚችለው ብቸኛው ቦምብ ነው።
የአሜሪካባለሥልጣናት በጥቃቱ ወቅት ኤምኦፒን ጥቅም ላይ መዋሉን ለሲቢኤስ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ዒላማ ሁለት ሁለት ቦምቦች ተጠቅመዋል።
