ካናዳ ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ልትጥል ነው

Date:

ካናዳ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች የማኅበራዊ ሚዲያን ለማገድ የሚያስችል ሕግ አቀረበች።

ሕጉ ባለፈው ዓመት በአውስትራሊያ ከጸደቀው ጋር ተመሳሳይ ነው ተብሏል።

ነገር ግን ከአውስትራሊያው ሕግ በተለየ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ታዳጊዎቹን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲዎች ካሏቸው ግዴታውስጥ አይገቡም።

ሕጉ የሰው ሠራሽ ቻትቦቶች እንዲሁም በኦንላየን “ያሉጎጂ ይዘቶችን” ለመከላከል ሰፊ እርምጃዎችን ይወስዳል ተብሏል።

ተቆጣጣሪዎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች  ሕጉን ማክበራቸውንእንዲከተተሉ ያደርጋል።

አንዳንድ የመናገር ነጻነት አቀንቃኞች ሳንሱርን ያስፋፋል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ሕጉ ለምክር ቤት የቀረበው በሚቀጥለው ሳምንት በፈረንሳይ ከሚካሄደው የቡድን ሰባት አገራት ስብሰባ በፊት ነው።

ይህ ደህንነቱ የተጠበቀ የማኅበራዊ ሚዲያ ረቂቅ ሕግ ረቡዕ ዕለት በባህል ሚኒስትር ማርክ ሚለር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ነበር።

በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ሚለር እንዳሉት “ልጆች እየሞቱ በመሆኑ”በኦንላየን የሚደርሱ ጉዳቶችን የሚመለከት ሕግ ማውጣትን የካናዳ መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

“ልጆች በዚህች አገር ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑንለማረጋገጥ ሁሉንም ተገቢ እርምጃዎች እንወስዳለን ማለት በቂ ነው” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...