“ወደ ሱዳን የሚላከው የኤለክትሪክ ሃይል በ80% ቀንሷል

Date:

በሱዳን ባለው የእርስበርስ ጦርነት ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ወደሀገሪቱ የምትልከው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ80 ከመቶ ያህል መቀነሱን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮያ በሰጡት ማብራሪያ፣ የሀገሪቱ የሃይል መሰረተልማት በእጅጉ በመጎዳቱ ይህ ሁኔታ መከሰቱን ገልፀዋል፡፡

አቶ ሞገስ መኮንን ፦

“ ከሱዳን ጋር የጠደረገው ስምምነት እስከ 100 ሜጋዋት ድረስ ለመላክ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን በመጠን ደረጃ በጣም ቀንሶዋል፡፡ ከ10 እስከ 20 ሜጋዋት ድረስ ነው እየላክን ያለነው፡፡ ዝቅ ሲል እስከ 10 ሜጋዋት፣ ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 20 ሜጋዋት ይሆናል የምንልከው፡፡

ይህ የሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተልማት በጦርነት በመጎዳቱ የመጣ ችግር ነው፡፡ ግጭቱ በጣም ከፍተኛ በሆነ መንገድ መሰረተልማቱን ጎድቶታል፡፡

ጦርነቱ እንደተቀሰቀሰ፣ መጀመሪያ ላይ 100 ሜጋዋት ሙሉውን ይወስዱ ነበር፡፡ ጦርነቱ እየተባባሰ ሲሔድ ግን ሃይል የመውሰድ ፍላጎታቸው እየቀነሰ መጣ፡፡ ችግሩ በአንዴ የመጣ አይደለም፣ በሒደት የመጣ ነው ” ብለዋል።

ይኸው ጦርነት በሚላከው የሃይል መጠን ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በክፍያ ላይም ተፅዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

“ ክፍያዎች ላይም አንዳንድ መዘግየቶች አሉ፣ መጠኑን ለመግለፅ ባልፈልግም፣ ከሱዳን ያልተሰበሰበ ሒሳብ አለን፡፡ ወደፊት መከፈል አለበት፣ መንግስትም ጣልቃ ይገባበታል ብለን እናስባለን፡፡ ሱዳኖቹ፣ አሁን ያለውን ችግራቸውን መፍታት ከቻሉ፣ ወደፊት እንደሚከፍሉ ይናገራሉ፡፡ እኛ ደግሞ እንደ መልካም ጎረቤት፣ ይህን ተቋቁመን እየላክን ነው፡፡ አለምአቀፍ ስምምነት ስላለ፣ በማንኛውም ሰዓት ለማስከፈል የሚከለክል ነገር የለም፡፡ ሀገሪቱ ሰላም እስክታገኝ ድረስ መላካችንን እንቀጥላለን ብለን እናምናለን ” ሲሉ ገልጸዋል።

በአሁኑ ጊዜ፣ ለጅቡቲ፣ ለኬንያ እና ለሱዳን የኤሌክትሪክ ሀይል የምትልከው ኢትዮጵያ፣ በመጪው ሚያዝያ ወር ለታንዛንያ ሃይል ማቅረብ እንደምትጀምርም አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡

“ ከታንዛኒያ ጋር ድንበር ስለማንጋራ፣ በኬንያ በኩል ነው ለሀገሪቱ ሃይል የምንልከው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ 2000 ሜጋዋት ኃይል የሚሸከም የማስተላለፊያ መስመር አለ፣ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ደግሞ አለ፡፡ ስዚህም ጉዳዩ የሶስትዮሽ ስምምነት ያስፈልገው ስለነበረ፣ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ከዛ በኋላ፣ ከኬንያ ጋር የሃይል ማስተላለፊያ ስምምነት፣ ከታንዛኒያ ጋር ደግሞ የሀይል ግዢ ስምምነት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተፈርሟል፡፡ በመጪው ሚያዝያ ወደ ታንዛኒያ 100 ሜጋዋት የኤሌአክትሪክ ሃይል መላክ ይጀመራል ” ሲሉ አሳውቀዋል።

ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊላንድም ተመሳሳይ ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን አቶ ሞገስ ገልፀው፣ በተለይም ለደቡብ ሱዳን ለመላክ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...