የሮማ ካቶሊካዊት ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

Date:


በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የጀርመን ፕረዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ቢያንስ የ130 ሐገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እንደተሳተፉ ታውቋል።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ከሐገራት መሪዎች እና ባለሥልጣናት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የተጓዙ ከ250,000 በላይ ሰዎች ተገኝተዋል።
በቀብራቸው ሥነ-ሥርዓት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በሃይማኖታዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮች የፈጸሟቸውን ዋና ዋና ተግባራት ተወስቷል። በተለይም ስደተኞች እና ድሆችን በመርዳት ያበረከቱት አስተዋፅኦ «ቁጥር ስፍር የሌለው» መሆኑን ተገልጿል።


በሌላ ዜና በቀብሩ ሥነስርዓት የተገኙት የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬይኑ ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ ተገናኝተው መነጋገራቸውን ታውቋል። የዋይት ሃውስ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ስቲቨን ቼንግ «ትራምፕ እና ዘለንስኪ ዛሬ ተገናኝተው ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል፤ ዝርዝር ጉዳዩ ወደ ፊትይገለጻል» ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...